Posts

Showing posts from 2010

ምንኩስና

Image
ታ ሪክ እንደሚያስረዳን ሄኖክ በተባሕትዎ ጀማሪነት መልከጼዲቅና ኤልያስ የድንግልና ሕይወትን ጀምረው ለድንግልና እብነት ወይም ምሳሌ መሆናቸውን፤ ዮሃንስ መጥምቅም ገና በህፃንነት ሳለ ሄኖክና ኤልያስን አብነት በማድረግ ሰላሳ ዘመን በገዳም ተወስኖ እህል ሳይበላ የወይን ጠጅ ሳይጠጣ የግመል ፀጉር ለብሶ ወገቡን በጠፍር መታጠቂያ ታጥቆ ጸንቶ ኖሯል። (ማቴ ፫፣፬/ ፲፣፲፭)

ጥቂት ስለ ጾም

ምንጭ:-  ከማህበረ ቅዱሳን በማሞ አየነው                ሰው የነፍስና የሥጋ ውህድ ፍጡር ነው፡፡ በመሆኑም የነፍሱን ጥም በቃለ እግዚአብሔር ሲያረካ እንደ ሥጋዊነቱ ደግሞ ሥጋዊ ምግብን ይመገባል ይጠጣል፡፡ በነፍስና በሥጋ መካከል ያለው መሠረታዊ ልዩነት ነፍስ ኢመዋቲ ሥጋ ደግሞ መዋቲ መሆናቸው ነው፡፡ በሌላ ገለጻ ሥጋ ያለነፍስ ሕይወት የላትም፡፡ ነፍስ ያለሥጋ ብቻዋን ጽድቅን እንደማትፈጽም ሁሉ ያለምግበ ሥጋም ሥጋ ቀዋሚ አይደለችም፡፡ ስለዚህም ነው ጽድቅ የነፍስና የሥጋ ጥምር ድርጊት የሆነ ነው፡፡  

Teach me how to pray!

Image
Lovely lady dressed in blue- Teach me how to pray! God was just your little boy, Tell me what to say,

‹‹ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡›› ማቴ 5፥10

                         በዲ/ን አሉላ መብራቱ ስደት፡- በቁሙ መስደድ ፣መሰደድ ፣መለየት፣ ቦታን መልቀቅ፣ ከሀገር ከዘመድ መራቅ፣ መፍለስ፣ መነቀል ማለት ነው፡፡ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ የተባሉት እውነትንና ጽድቅን ለማወቅ ወይም ለማስተማር ወይም በምናኔ ምክንያት ሀገራቸውን ጥለው የተሰደዱ፣ እውነትን በመናገራቸው ስለ እውነተኛይቱ ሃይማኖት በመቆማቸው፣ በእግዚአብሔርና በምዕመናን ፊት ሞገስንና መወደድን በማግኘታቸው ምክንያት በመናፍቃን፣ የራሳቸውን ክብር በሚፈልጉ ቀናተኞች ወይም በአላውያን ነገሥታት የተሰደዱትን ነፍሳቸውንና ሥጋቸውን ሊያጠፉ ከተነሱት አካላት የሸሹትን፣ ከምንፍቅናና ከስህተት አስተሳሰቦች ራሳቸውን የለዩና ያሸሹትን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ

Image
ዲያቆን ታደሰ ወርቁ እነዚህ ሁለት ቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስት ቤተክርስቲያናችን አዕማድ ናቸው፡፡ በመሠረትነት በአጸኗት ቤተክርስቲያን ያላቸው የክብር ሥፍራ ላቅ ያለ ነው፡፡ ይህ የሆነው እንዲሁ አይደለም፡፡ ለቤተክርስቲያንና በቤተክርስቲያን የፈጸሙት አገልግሎት በዚህም የተቀበሉት ሰማዕትነት ነው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትም ይህን መልካም የሆነውን ታሪካቸውን ለእኛ አርአያነት በሚሆን መልኩ ከትበውልናል፡፡ እኛም ለአርአርያነት በሚሆን መልኩ የእነዚህን ደጋግ ሁለት ቅዱሳን አባቶች ታሪክ፣ ዕውቀትና መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ከዚህ በመቀጠል አቅርበናል፡፡ 1. ሁለቱ ሐዋርያት ሲጠሩ የነበሩበት ሕይወት ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተ ሳይዳ ሲወለድ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ ደግሞ በጠርሴስ ከተማ ተወለደ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ ደግሞ በ 15 ዓመት ዕድሜው በገማልያ ትምህርት ቤት በመግባት የአይሁድን ሕግና ሥርዓት ተምሯል፡፡ በ30 ዓመቱም የአይሁድ ሸንጎ አባል ሆኗል፡፡ /1ቆሮ.1.17፤ሐዋ.22.3/

«ሐነጸ መቅደሶ በአርያም፤ መቅደሱን በአርያም /በልዕልና/ አነጸ»

በዲ / ን በረከት አዝመራው ሰኔ 20 እና 21 በእመቤታችን ስም በፊልጵስዩስ የታነጸችው የቤተክርስቲያን መታሰቢያ በዓል ነው፡፡ ይህች ሃገር ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ ተዘዋውረው ያስተማሩባትና ብዙ ምዕመናንን ያፈሩባት ቦታ ናት፡፡ ከዚያም በኋላ በዚህች ቦታ የመጀመሪያዋ በእመቤታችን ስም የታነጸች ቤተ ክርስቲያን መተከሏን የሰኔ 20 ስንክሳርና ሌሎችም ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ምሥጢራዊ /mystical/ መልዕክቶች ከብዙ በጥቂቱ ማብራራት ነው፡፡ እያንዳንዱ ምዕመን እንደ ጥረቱና እንደ መንፈሳዊ እይታው ብዙ ድንቅ መልዕክቶችን ቢያገኝም ከብዙ ጥቂቱ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና ማኅበረ ምዕመናን በግእዝና በአማርኛው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ « ቤተ ክርስቲያን » ተብሎ ተተርጉሞ የምናገኘው « አቅሌስያ » የሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም « የኅሩያነ እግዚአብሔር ፣ የምዕምናን አንድነት » ማለት ነው፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህ ስም ከማኅበረ ምዕመናን በተጨማሪ ለሕንፃ ቤተ ክርስቲያንም ይሰጣል፡፡ ይህም ሐዋርያዊ ትውፊት ነው፡፡ በሐዋርያት ዘመን ምዕምናን የሚገናኙበት ቤትም ፣ የምዕምናኑ አንድነትም « ቤተ ክርስቲያን » እየተባለ ይጠራ ነበር / ሮሜ 16.5 ፣ 1 ቆሮ . 11.8/ ፡፡ ዛሬም ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን ይህን ትውፊት ጠብቃ ሕንፃውንም ማኅበረ ክርስቲያኑም « ቤተ ክርስቲያን » እያለች ትጠራለች፡፡ የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ሕይወት ረቂቅና ምጡቅ፣ በመንፈስ ...