Posts

Showing posts from June, 2010

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13

1 በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ። 2 ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። 3 ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። 4 ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ 5 የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ 6 ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ 7 ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። 8 ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል። 9 ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና፤ 10 ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል። 11 ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ። 12 ...

«በንስርም ክንፍ እንደተሸከምኋችሁ፤ ወደ እኔም እንዳመጣችሁ አይታችኋል!»

Image
ንስር ንጉሠ አዕዋፍ ነው፤ በመብረርም ፈጣንና ጠንካራ የሆነ ነው፡፡ ረዥም ዘመን የሚኖር፣ ከሩቅ አጥርቶ የሚያይ፣ እስከ ተራሮች ከፍታና ከደመናት በላይ ለመብረር የሚያስችሉ ኃያላን አክናፍ ያሉት ነው፡፡ እንዲሁም ንስር ለጫጩቶቹ ርኅሩኅ ነው፡፡ በጥበብ ይንከባከባቸዋል ራሳቸውን ችለው እንዲቆሙም ያለማምዳቸዋል፡፡ ከእነዚህ ተነጻጻሪ ባሕርያት የተነሣ እግዚአብሔር በትሕትና ራሱን ከንስር ጋር አመሳስሏል፡፡ እግዚአብሔር ዘላለማዊ፣ ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን ተመልካች (ሁሉን የሚያይና የሚያውቅ የጥበብ ምንጭ)፣ ምሕረትን የተሞላ፣ ለሕዝቡ የሚራራና ወደ ድኅነት የሚመራቸው ነው፡፡ ጌታ እግዚአብሔር ሕዝቡን መርቶ ከግብፅ ባወጣቸውና ከፈርኦን ሠራዊት ጠብቆ በተአምር ቀይ ባሕርን ባሻገራቸው ጊዜ እንዲህ ብሏቸው ነበር፡- ‹‹በግብፃውያን ያደረግሁትን በንስርም ክንፍ እንደተሸከምኋችሁ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል›› (ዘጸ. 19፥4)፡፡ በንስር ሕይወት ውስጥ ካሉት ምሥጢራት አንዱ ሁልጊዜ ጎጆውን በከፍታ ላይ መሥራቱና በአለታማ ቋጥኞችና ምሽጎች ውስጥ መኖሩ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለኢዮብ ጥበቡንና ኃይሉን ሲያሳየው ያለውን ልብ በሉ፤ ‹‹በአፍህ ትእዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላልን? ቤቱንስ በአርያም ላይ ያደርጋልን? በገደል ላይ ይኖራል፤ በገደሉ ገመገምና በጥጉ ያድራል፡፡ በዚያም ሆኖ የሚነጥቀውን ይጎበኛል፤ ዓይኑም በሩቅ ትመለከታለች፡፡›› (ኢዮ.39፥27) ንስር ስለምን ከፍ ብሎ ጎጆውን በተራሮች ጫፍ ላይ ይሠራል? እንደ አዳኞችና አራዊት ያሉ ጠላቶቹ ሊደርሱበት ከማይችሉበት ስፍራ ለመገኘት ብሎ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ወደ ጎጆው ደርሶ ጫጩቶቹን ሊበላበት የሚችል ሌላ ጠላት አለ፡፡ ይህም ጠላት እስከዚያ ከፍታ ድረስ እስኪደርስ በልቡ ሊሳብ የሚችለው ዕባብ ነው፡፡ ታዲያ ይህንን ው...

ገንዘብና ክርስቲያናዊ ሕይወት /ከቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ/

- ገንዘብ ለመግዛት ለመሸጥ ለመለወጥ የምንጠቀምበት በሕይወታችንም የራሱ ሚና ያለው ነው፡፡ - በዓለማችን ለሚከሰቱ በርካታ ግጭቶች ዋነኛው መንሥኤ ነው፡፡ - ገንዘብን እንዳናመልክ፣ ርኅራኄን የምናስተላልፍበትና በጎውን ፈቃድ እንድንፈጽምበት ቅዱስ መጽሐፍ የሚሰጠን መመሪያዎች አሉ፡፡ መመሪያዎቹ ምንድን ናቸው? 1. ገንዘብ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው - “ደስም እንዲለን እግዚአብሔር ሁሉን አትርፎ ሰጠን፡፡” 1ኛ ጢሞ 6፡17፡፡ - “ከሰማይ በታች ያለው ሁሉ ገንዘቤ ነው፡፡” ኢዮብ 41፡3፡፡ - እግዚአብሔር ከገንዘብ አስቀድሞ ሕይወትንና ጤንነትን ሰጥቶናል፡፡ በነዚህም አማካይነት ገንዘብ የምናገኝባቸውን የጉልበት፣ የሞያ ወዘተ ሥራ እንሠራለን፡፡ - ስለዚህ ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለድሆች በምንሰጥበት ጊዜ ሁሉ “ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃል፡፡” ቀዳ ዜና 29፡14፡፡

ይህን ያዉቃሉ?

Image
ቤተክርስቲያንናችን የምታምነዉና የምታስተምረዉ የክርስትና እምነትና ሥርዓተ-አምልኮት ይህ መሆኑን፦ 1. ህልወተ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር መኖር) ስሙና የስሙ ትርጉም ፈጣሪነቱ ጌትነቱ (የባህርይ) አምላክነቱ ንጉስነቱ (የባህርይ) ሁሉን የያዘ ሁሉን የጨበጠ መሆኑ ሁሉን የጀመረ ሁሉን የጨረሰ መሆኑ ዘለዓለማዊነቱ ሁሉን ቻይነቱ በዓለም ምልዓቱ ሁሉን አዋቂነቱ (የባህርይ) ጥበበኛነቱ (የባህርይ) ሕያዉነቱ ኃያልነቱ (የባህርይ) ረቂቅነቱ(የማይታይ መሆኑ) መሐሪነቱ (ሁሉን ይቅር ባይ) ቅዱስነቱ (የባህርይ) በእዉነት የሚገዛና የሚፈርድ መሆኑ የሰዉ ወዳጅ መሆኑ (መፍቀሬ ሰብእ) ትዕግስተኛነቱ መምህርነቱ (የባህርይ) ብርሃንነቱ (የባህርይ) አዳኝነቱ መጋቢነቱ ጠባቂነቱ ረዳትነቱ ባለፀጋነቱ (የባህርይ) ...