ይህን ያዉቃሉ?



ቤተክርስቲያንናችን የምታምነዉና የምታስተምረዉ የክርስትና እምነትና ሥርዓተ-አምልኮት ይህ መሆኑን፦
1. ህልወተ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር መኖር)
ስሙና የስሙ ትርጉም
ፈጣሪነቱ
ጌትነቱ (የባህርይ)
አምላክነቱ
ንጉስነቱ (የባህርይ)
ሁሉን የያዘ ሁሉን የጨበጠ መሆኑ
ሁሉን የጀመረ ሁሉን የጨረሰ መሆኑ
ዘለዓለማዊነቱ
ሁሉን ቻይነቱ
በዓለም ምልዓቱ
ሁሉን አዋቂነቱ (የባህርይ)
ጥበበኛነቱ (የባህርይ)
ሕያዉነቱ
ኃያልነቱ (የባህርይ)
ረቂቅነቱ(የማይታይ መሆኑ)
መሐሪነቱ (ሁሉን ይቅር ባይ)
ቅዱስነቱ (የባህርይ)
በእዉነት የሚገዛና የሚፈርድ መሆኑ
የሰዉ ወዳጅ መሆኑ (መፍቀሬ ሰብእ)
ትዕግስተኛነቱ
መምህርነቱ (የባህርይ)
ብርሃንነቱ (የባህርይ)
አዳኝነቱ
መጋቢነቱ
ጠባቂነቱ
ረዳትነቱ
ባለፀጋነቱ (የባህርይ)
አባትነቱ (የባህርይ)
ይህን የመሳሰለ ግብሩ እየተተነተነ፤

2. ሥነ ፍጥረት ከእሁድ እስከ አርብ ሰማይና በሠማይ የሚኖሩትን ምድርንና በምድር የሚኖሩትን
ባህርና በባህርየሚኖሩትን ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር መሆኑን በመንገር የፍጥረቱን
ስርዓት በመተንተን ቤተ ክርስቲያናችን ታስተምራለች ።

3. 5ቱ አዕማደ ሚስጥራት
ምስጠረ ስላሴ
ምስጠረ ስጋዊ
ምስጠረ ጥምቀት
ምስጠረ ቁርባን
ምስጠረ ትንሳኤ

4. 7ቱ ሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያን
ምስጠረ ጥምቀት
ምስጠረ ሜሮን
ምስጠረ ቁርባን
ምስጠረ ንስሃ
ምስጠረ ተክሊል
ምስጠረ ክህነት
ምስጠረ ቀንዲል ከነስርዓቱ በትምህርትና በተግባር

5. ነገረ ማርያም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ታሪክና ክብር ንፅህና ቅድስናና ምርጫ አማላጅነት
6. ክብረ ቅድሳን ክብራቸዉና አማላጅነታቸዉ ቃል ኪዳናቸዉ
7. ቤተ ክርስትያን አንዲት መሆናን ቅድስት መሆናን
8. ስለ ፅላትና ታቦት ከነስርዓቱ ትምህርት ይሰጣል ። ይታመናል።
9. ስለ ስዕል ያለዉ ስርዓት ይነገራል ይታመናል
10. ስለ መስቀል ያለዉ ስርዓት ይነገራል ይታመናል ትምህርት ይሰጣል
ይህን በመሠለ መልኩ ቤተ ክርስቲያናችን ታስተምራለች።
እኛስ

የተማርነውን የት ጠፋ?

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ከክርስቶስ ልደት እስከ 2000

Comments

  1. እጅግ በጣም ጥሩ ጽሁፍ ነው::እግዚአብሄር ይባርካችሁ!!

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular posts from this blog

ቅዱስ ያሬድ ማነው? ከዳንኤል ክብረት

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፬ የሐዲስ ኪዳን መግቢያ

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፪