ገንዘብና ክርስቲያናዊ ሕይወት /ከቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ/

- ገንዘብ ለመግዛት ለመሸጥ ለመለወጥ የምንጠቀምበት በሕይወታችንም የራሱ ሚና ያለው ነው፡፡
- በዓለማችን ለሚከሰቱ በርካታ ግጭቶች ዋነኛው መንሥኤ ነው፡፡
- ገንዘብን እንዳናመልክ፣ ርኅራኄን የምናስተላልፍበትና በጎውን ፈቃድ እንድንፈጽምበት ቅዱስ መጽሐፍ
የሚሰጠን መመሪያዎች አሉ፡፡ መመሪያዎቹ ምንድን ናቸው?
1. ገንዘብ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው
- “ደስም እንዲለን እግዚአብሔር ሁሉን አትርፎ ሰጠን፡፡” 1ኛ ጢሞ 6፡17፡፡
- “ከሰማይ በታች ያለው ሁሉ ገንዘቤ ነው፡፡” ኢዮብ 41፡3፡፡
- እግዚአብሔር ከገንዘብ አስቀድሞ ሕይወትንና ጤንነትን ሰጥቶናል፡፡ በነዚህም
አማካይነት ገንዘብ የምናገኝባቸውን የጉልበት፣ የሞያ ወዘተ ሥራ እንሠራለን፡፡
- ስለዚህ ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለድሆች በምንሰጥበት ጊዜ ሁሉ “ሁሉ ከአንተ ዘንድ
ነውና ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃል፡፡” ቀዳ ዜና 29፡14፡፡

2. ገንዘብ የሰው መላ ሕይወት አይደለም
- ሰው በገንዘብ መኖር የሚኖር ባለመኖሩም የማይኖር አይደለም፡፡
- ሕይወትም በገንዘብ መኖር የሚሠምር በገንዘብ አለመኖርም የሚጠፋ አይደለም፡፡
- “የሰው ሕይወቱ በገንዘቡ ብዛት አይደለምና እንዳትሰቱ ተጠንቀቁ። ” ሉቃ 12፡15፡፡
- “በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን፡፡” የሐ ሥራ 17፡28፡፡
3. ገንዘብ የእውነተኛ ደስታ ምንጭ አይደለም
- “ጥል ባለበት እርድ ከሞላበት ቤት በጸጥታ ደረቅ ቁራሽ ይሻላል፡፡ ” ምሳሌ 17፡1፡፡
- በገንዘብ ደስታ አይገዛምና ይኽንን ለማድረግ የሚጣጣሩ ሁሉ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል፡፡
4. ገንዘብ አላፊ ጠፊ ነው
- “በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ፥ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው
እግዚአብሔር እንጂ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።” 1ኛ ጢሞ 6፡17-19፡፡
- በገንዘብ መታመን ድንገተኛ የሆነ የአእምሮ መናወጥና መታወክ እንዲሁም ድንጋጤን
ያስከትላል፡፡
5. ገንዘብ መመዘኛ (መለኪያ) ነው
- ገንዘብን ለእግዚአብሔር ክብር ማዋል ይገባል፡፡
- “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው። ” የሐዋ ሥራ 20፡35፡፡
- ገንዘብ ከእግዚአብሔር በአደራ የተሰጠን እንጂ የራሳችንም አይደለም፡፡ ሉቃ 16፡1-15፡፡
- “ሰካርና ሆዳም ይደኸያሉ፡፡” ምሳ 23፡21፡፡
6. በገንዘብ አትመካ
- በገንዘብ መመካት እግዚአብሔርን መካድ ነው፡፡
- “በገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው?። ” ማር 10፡24፡፡
- “ወርቅን ተስፋ አድርጌ እንደሆንሁ… እጄም ስላላገኘች ደስ ብሎኝ እንደሆነ… ልቤ በስውር
ተታልሎ… ልዑል እግዚአብሔርን በካድሁ ነበር፡፡” ኢዮብ 31፡24-28፡፡
- ገንዘብን የሕይወት ምሰሶ አድርጎ ማሰብ ችግር ያስከትላል፡፡
- “በባለጠግነቱ የሚታመን ሰው ይወድቃል፡፡” ምሳሌ 11፡28፡፡
7. ገንዘብ በአግባቡ ካልተጠቀሙበት ያሰናክላል
- “ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ
ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥
ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ። አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤
ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።”
1ኛ ጢሞ 6፡9-10፡፡
- ጌታችንም የገንዘብ ፍቅር ከአምልኮተ እግዚአብሔር ጋር እንደሚጣላ ሲገልጥ “Aንድ ባሪያ ለሁለት ጌቶች
መገዛት አይቻለውም፡፡” ሉቃ 16፡13፡፡
8. ያለን ይበቃናል እንበል
- ሰዎች ሁልጊዜ ራሳችንን ለማሻሻል መፈለጋችን የሚበቃንን ለማግኘት ሆኖ ለቅንጦት ካልሆነ መልካም ነው፡፡
“ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው እግዚAብሔርን መምሰል ማትረፊያ ነው። ” 1ኛ ጢሞ 6፡6፡፡
- “መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ በእርሱሰም ታመን እርሱም ይደግፍሃል፡፡” መዝ 36(37)፡5፡፡
- “አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለመውደድ ይሁን ያላችሁም ይብቃችሁ፡፡” ኢዮብ 13፡5፡፡
- ያላችሁ አንሶ እንደሆነ “እግዚአብሔር ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ
ትበዙ ዘንድ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል፡፡ ” 2ኛ ቆሮ 9፡8፡፡
- ዋናው ነገር “የዕለት እንጀራችንን ለዛሬ ስጠን።” ማለት ነው መጠኑን እርሱ ያውቀዋልና፡፡ ማቴ 6፡11፡፡
- “ቅምጥሊቱ ግን በሕይወትዋ ሳለች የሞተች ናት፡፡” 1ኛ ጢሞ 5፡6
9. ገንዘባችንን የምናስተዳድርበት ሥርዓት ይኑረን
- ክርስቲያኖች ገንዘባቸውን የሚያስተዳድሩበት ሥርዓት ሊኖራቸውና ከሚያገኙትም በላይ እንዳያወጡ
ሊጠነቀቁ ይገባል፡፡ ገንዘባችንን በሥርዓት ለማስተዳደር የሚከተሉትን መንገዶች መከተል ይቻላል፡፡
1. ለእግዚአብሔር (አሥራት)
2. ለየራሳችን ወጪ (ለባልም ሆነ ለሚስት)
3. ለቤተሰብ (ለቀለብ...)
4. ለልጆች ወጪ
5. ለወላጆቻችን
6. ለቁጠባ (እግዚአብሔር የሚወደውን እንድንሠራበት፣ ባስፈለገንም ጊዜ ለሚጠቅመን እንድናውለው...)
10. ተጨማሪ ምክሮች ከቅዱስ መጽሐፍ
- “ሁለትን ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ሳልሞትም አትከልክለኝ ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው ድኅነትንና ባለጠግነትን
አትስጠኝ ነገር ግን የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ፥ እንዳልጠግብ እንዳልክድህም። እግዚአብሔርስ ማን ነው? እንዳልል ድሀም
እንዳልሆን እንዳልሰርቅም፥ በአምላኬም ስም በሐሰት እንዳልምል። ” ምሳሌ 30፡7-9፡፡
- “መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ በእርሱሰም ታመን እርሱም ይደግፍሃል፡፡” መዝ 36(37)፡5፡፡
- “ጻድቅ ሲራብ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም ሁልጊዜም ይራራል ያበድርማል ዘሩም በበረከት ይኖራል፡፡”
መዝ 36(37)፡25-36፡፡
- “በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ”
ፊል 4፡6፡፡
- “እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ። እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና
የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።” 1ኛ ጴጥ 5፡6-7፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ቅዱስ ያሬድ ማነው? ከዳንኤል ክብረት

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፬ የሐዲስ ኪዳን መግቢያ

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፪