ምንኩስና

ሪክ እንደሚያስረዳን ሄኖክ በተባሕትዎ ጀማሪነት መልከጼዲቅና ኤልያስ የድንግልና ሕይወትን ጀምረው ለድንግልና እብነት ወይም ምሳሌ መሆናቸውን፤ ዮሃንስ መጥምቅም ገና በህፃንነት ሳለ ሄኖክና ኤልያስን አብነት በማድረግ ሰላሳ ዘመን በገዳም ተወስኖ እህል ሳይበላ የወይን ጠጅ ሳይጠጣ የግመል ፀጉር ለብሶ ወገቡን በጠፍር መታጠቂያ ታጥቆ ጸንቶ ኖሯል። (ማቴ ፫፣፬/ ፲፣፲፭)

       ምንኩስና በመንፈሰ እግዚአብሔር የተመራ ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ እንዳስተማረው “ቤቱን ወንድሙንና እህቱን አባቱንና እናቱን ሚስቱንና ልጆቹን ንብረቱን ትቶ በስሜ አምኖ ይከተለኝ። የዚህን ሁሉ መቶ እጥፍ ያገኛል የዘላለም ድህነትም ያገኛል።” (ሉቃ ፱፣፹፪) በማለት የምንኩስናን ዋጋና ትርጉም እስረድቶናል። ከሴት እርቄ ንጽህናየን ጠብቄ መኖርን እፈቅዳሁ ብሎ ሰውነቱን ለእግዚአብሄር አደራ የሰጠ ሰው መነኩሴ ሲባል የምንኩስና ጀማሪውም አባ እንጦስ ሲሆን የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያንም ይህንን መሰረት በማድረግ ገዳማትና መናንያን ከትውልድ ወደ ትውልድ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሲተላለፍ ቆይቷል። ወደ ፊትም እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ ጸንቶ ይኖራል።
     ምንኩስና በአለባበስም የተለየ ሲሆን ምሳሌውም ከጌታችን ኢየሱስ የተገኘ ነው። ቆቡ የእክሊለ ሶክ፣ ቀሚሱ የከለሜዳ፣ ቅናቱ የሐብል፣ ስጋ ማርያም የማርያም ስጋና እስኬማው በሰውነቱ መስለን እንደተናገርነው ሰው የመሆኑ ምሳሌ ነው።  ልብሰ ምንኩስና ጥንታዊ ምሳሌ የያዘ ሲሆን ምክንያቱን አንደሚከተለው እንመለከታለን።
1 እስራኤል ከግብጽ በወጡ ጊዜ ኩፋት ደፍተው፣ በሎታ ይዘው፣ ዝናር ታጥቀውና ጫማ አዝበው እንደ ተነሱ መነኮሳትም እንዲህ ለብሰው በምናኔ ከዚያም በሞት ይህችን አለም ይለያሉ።
2 በብሉይ ሊቀ ካህናቱ በውስጥ እጀ ጠባብ በላይ እጀ ሰፊ ከዚያም በላይ እንደ መብርህት ያለ ይደርብ ነበር። ይንንም ለብሶ አፍአዊ መሥዋዕት ይሰዋና የአፍአዊ ሃጢያትን ያስተሰርያል። መነኮሳትም እንዲህ ያለ ልብሰ ምንኩስና ለብሰው ውስጣዊ መስዋዕትን ይሰውና ውስጣዊ ሃጢያትን ያስተሰርያሉ።
3 መነኮሳት ልብሰ ምንኩስና ለብሰው ረቂቅ ጠላታችንን ሰይጣንን ድል በነሱ ጊዜ ስላሴ የብርሃን ካባ ላንቃ ያለብሷቸዋል። ይህም አንድ የበቃ መነኩሴ አንዳየው ሲሆን የበቃ መነኩሴ ሶስት የብርሃን ካባ ላንቃ ሲወርድ አይቶ መልአኩን ቢጠይቀው አንዱ ባሕታዊ ዘበሕድአት፣ ሁለተኛው ድውይ ዘበአኮቴት እንዲሁም ሦስተኛው ረድእ ዘበጥብአት የሚያገኙበት የክብር ልብስ ነው ብሎ አስረድቶታል።
        የዋህ ጳውሊ ቃል እንደተገለጸው፤ የዋህ ጳውሊና አባ እንጦንስ በፈቃደ እግዚአብሄር ተገናኝተው ነገረ እግዚአብሄርን ሲነጋገሩ ከሰነበቱ በኋላ  የዋህ ጳውሊ በአባ እንጦስ ራስ ላይ ቆብ አይቶ ይህንስ እንዴት አገኘኸው ብሎ ቢጠይቀው አባ እንጦስም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰጠኝ አለና በፈጣሪ ፈቃድ እንዳገኘው ነገረው። በዚህም ጊዜ የዋህ ጳውሊ የጌታን ቸርነት እያደነቀ በተመስጦ አግዚአብሄርን አመሰገነ።
ለመሆኑ የመነኮሳቱ አመጋገብ እንዴት?
ይቀጥላል....

Comments

Popular posts from this blog

ቅዱስ ያሬድ ማነው? ከዳንኤል ክብረት

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፬ የሐዲስ ኪዳን መግቢያ

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፪