Posts
Showing posts from 2011
ውግዘት የሚገባው ተግባር
- Get link
- X
- Other Apps
በዘመናት ታሪክ ውስጥ በእግዚአብሔር ዘንድ መጸጸትን፣ የቁጣ ጅራፍን፣ መዓትንና እጅግ መራራ ቅጣትን ካስከተሉ እኩያን ተግባራት መካከል ተፈጥሮ ከሚያዘው ውጪ ወንዶች ከወንዶችና ሴቶች ከሴቶች ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት ወይም ግብረ ሰዶማዊነት አንዱ ነው፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት ስያሜውን ያገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ድርጊቱን በፈጸሙ ሕዝቦች አገር ስም ነው፡፡ ይህ ኃጢአት በተለይ በሰዶም ይበዛ ስለነበር ግብረ ሰዶም ተብሏል፡፡ ሰዶምና ጐረቤቷ ገሞራ በዮርዳኖስ ሸለቆ አካባቢ የተቆረቆሩ ከተሞች ነበሩ፡፡ Read More........
- Get link
- X
- Other Apps
የሴት ራስ - ወንድ by Birhanu Admass Anleye እንደምን ሰነበታችሁ፡፡ ረዘም ላለ ጊዜ በመጥፋቴ ይቅርታ እየጠየቅሁ ለጊዜዉ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የሃይማኖት ዐምድ ‹‹ሃይማኖት እና ሴቶች›› በሚለዉ የመወያያ ርእሰ ጉዳይ ላይ ከእኛ እምነት አንጻር ያቀረብኳትን ትንሽ መጣጥፍ እነሆ ብያለሁ፡፡ ቤልጄየም ዉስጥ በምትገኘዉ የአንትወርፕ ከተማ አይሁድ ይበዙባታል፡፡ በዚሁ ምክንያት በዚያ ሀገር ሱቆች እንኳ ሳይቀር በብዛት የሚይዙት ለአይሁድ የሚሆኑትን ልብሶችና ሌሎች የእነርሱን ፍላጎት የሚያሟሉ ነገሮች ነዉ፡፡ ምክንያቱም በዚያ ለሁለት ሺሕ ዐመታት በተሰደዱባቸዉ ቦታዎችም ባሕላቸዉንንና ዕሴቶቻቸዉን ጠብቀዉ የሚኖሩ በመሆናቸዉ ነዉ፡፡ የተማሩት ትምህርትና የደረሱበት ሥልጣኔና ዘመናዊነት ምንም ያህል ተጽእኖ እንዳያመጣ አድርገዉ መቛቛማቸዉም ሥልጣኔና ዕሴትን አንዴት አስታርቆ መሔድ እንደሚቻልም ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡ Read More.....
ደብረ ታቦር
- Get link
- X
- Other Apps
ይህ በዓል በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ የሚከበር ሲሆን ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ አያሰተማረ በነበረበት ዘመን በደብረ ታቦር ላይ ብርሃነ መለኮቱን ክበረ መንግስቱን የገለጸበት እለት ነው። /ማቴ ፲፯፥፩/ ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ስም አለው ቡሄ ይሉታል ቡሄ ማለት መላጣ ገላጣ ማለት ሲሆን ይህን ስያሜ ያገኘው ክረምቱ አልቆ ደመናው ተገልጦ ብርሃን የሚታይበት ጊዜ ስለሆነ ነው ተብሎ ይነገራል። ነገር ግን የደብረ ታቦር ምስጢር የተገለጸው በፍልስጥኤም ደመና በማይታይበት በበጋ ወራት ነው።
ልጅህ
- Get link
- X
- Other Apps
Ø እንደ ቃየል በቅናት ካደገ የገዛ ወንድሙን ይገድላል። /ዘፍ 4፤5/ Ø እንደ ካም ካደገ ያንተኑ ሃፍረት ይገልጥብሃል። /ዘፍ 9፤21-22/ Ø እንደ ዲና ካደገች ሂዳ ከጠላቶችህ ትወዳጃለች። /ዘፍ 34፤1/ Ø እንደ ዔሳው ካደገ ምቀኛ ይሆንብሃል። /ዘፍ 27፤41-45/ Ø እንደ ይሁዳ ልጆች ካደገ የከፋ ይሆንብሃል። /ዘፍ 38፤1-11/ Ø እንደ ሮቤል ካደገ ሚስትህን ይቀማሃል። /ኩፍ 28፤35-44/ Ø እንደ አፍኒንና ፊንሐስ ካደገ ታቦት ሻጭ ይሆንብሃል። /1ኛ ሳሙ 2፤12/ Ø እንደ አምኖን ከደገ የገዛ እህቱን ይደፍርብሃል። /2ኛ ሳሙ 13፤1-19/ Ø አንደ አቤሴሎም ካደገ አንተንም ያሳድድሃል። /2ኛ ሳሙ 17፤21-24/ Ø አንደ ሴምና ያፌት ከደገ ሃፍረትህን ይደብቅልሃል። /ዘፍ 9፤23/ Ø አንደ ዮሴፍ ካደገ በችግርህ ደራሽ ይሆንልሃል። /ዘፍ 39፤7-23/ Ø እንደ ይስሐቅ ካደገ ታማኝ ሆኖ ራሱን ይሰዋል። /ዘፍ 22፤9/ Ø እንደ ሳሙኤል ካደገ የእግዚአብሔር ሰው ይሆንልሃል። /1ኛ ሳሙ 3፤17-20/ Ø እንደ ዳዊት ካደገ የአገርህን ጠላት ያጠፋልሃል ፤ በሰው በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ ይሆንልሃል። /1ኛ ሳሙ 17፤34-54/ ልጆች ቢኖሩህ ምከራቸው ፤ ከሕጻንነታቸው ጀምረህ ሰቢረ ክሳድን አስተምራቸው። /ሲራ 7፤23 ና 17፤1-4/ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንኩስና ክፍል ፪
- Get link
- X
- Other Apps
ለመሆኑ የመነኮሳቱ አመጋገብ እንዴት ነው ? መነኮሳቱ የሚመገቡት፦ ቋርፍ ወይም ስራስር ተቆፍሮ የሚገኝ ንፍሮ፣ዳቤ ወይም መኮሬታ፣ ቅጠላ ቅጠል፣ ቆሎ የመሳሰሉትን እንደ ገዳሙ ስርዓት መሰረት በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ዘጠኝ ወይም ሶስት ሰዓት ላይ ብቻ ይመገባሉ። አለባበስ፦ መነኮሳት በምድር መላእክት በሰማይ ሰዎች ናቸው ስለዚህ በዚህ አስተሳሰብ ከዓለማዊያን እንደተለዩ ሁሉ በአለባበስም እንዲሁ ይለያሉ ። አለባበሳቸው መነኮሳት ቢጫ ወይም ወይባ መልክ ያለው፣ ጥቁርና የማር መልክ ያለው ምክንያቱም ከዓለም የተለዩ፣ ዓለምን ንቀውና ንፅህናቸውን ጠብቀው መኖርን ስለመረጡ በሥጋ ደክመው በመንፈስ የበረቱ ማለት ሲሆን በዓለማውያን ዘንድ የተናቀ የተጠላ መልበሰን መረጡ የሚሉ አሉ።