ምንኩስና ክፍል ፪
ለመሆኑ የመነኮሳቱ አመጋገብ እንዴት ነው ? መነኮሳቱ የሚመገቡት፦ ቋርፍ ወይም ስራስር ተቆፍሮ የሚገኝ ንፍሮ፣ዳቤ ወይም መኮሬታ፣ ቅጠላ ቅጠል፣ ቆሎ የመሳሰሉትን እንደ ገዳሙ ስርዓት መሰረት በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ዘጠኝ ወይም ሶስት ሰዓት ላይ ብቻ ይመገባሉ። አለባበስ፦ መነኮሳት በምድር መላእክት በሰማይ ሰዎች ናቸው ስለዚህ በዚህ አስተሳሰብ ከዓለማዊያን እንደተለዩ ሁሉ በአለባበስም እንዲሁ ይለያሉ ። አለባበሳቸው መነኮሳት ቢጫ ወይም ወይባ መልክ ያለው፣ ጥቁርና የማር መልክ ያለው ምክንያቱም ከዓለም የተለዩ፣ ዓለምን ንቀውና ንፅህናቸውን ጠብቀው መኖርን ስለመረጡ በሥጋ ደክመው በመንፈስ የበረቱ ማለት ሲሆን በዓለማውያን ዘንድ የተናቀ የተጠላ መልበሰን መረጡ የሚሉ አሉ።