Ø እንደ ቃየል በቅናት ካደገ የገዛ ወንድሙን ይገድላል። /ዘፍ 4፤5/ Ø እንደ ካም ካደገ ያንተኑ ሃፍረት ይገልጥብሃል። /ዘፍ 9፤21-22/ Ø እንደ ዲና ካደገች ሂዳ ከጠላቶችህ ትወዳጃለች። /ዘፍ 34፤1/ Ø እንደ ዔሳው ካደገ ምቀኛ ይሆንብሃል። /ዘፍ 27፤41-45/ Ø እንደ ይሁዳ ልጆች ካደገ የከፋ ይሆንብሃል። /ዘፍ 38፤1-11/ Ø እንደ ሮቤል ካደገ ሚስትህን ይቀማሃል። /ኩፍ 28፤35-44/ Ø እንደ አፍኒንና ፊንሐስ ካደገ ታቦት ሻጭ ይሆንብሃል። /1ኛ ሳሙ 2፤12/ Ø እንደ አምኖን ከደገ የገዛ እህቱን ይደፍርብሃል። /2ኛ ሳሙ 13፤1-19/ Ø አንደ አቤሴሎም ካደገ አንተንም ያሳድድሃል። /2ኛ ሳሙ 17፤21-24/ Ø አንደ ሴምና ያፌት ከደገ ሃፍረትህን ይደብቅልሃል። /ዘፍ 9፤23/ Ø አንደ ዮሴፍ ካደገ በችግርህ ደራሽ ይሆንልሃል። /ዘፍ 39፤7-23/ Ø እንደ ይስሐቅ ካደገ ታማኝ ሆኖ ራሱን ይሰዋል። /ዘፍ 22፤9/ Ø እንደ ሳሙኤል ካደገ የእግዚአብሔር ሰው ይሆንልሃል። /1ኛ ሳሙ 3፤17-20/ Ø እንደ ዳዊት ካደገ የአገርህን ጠላት ያጠፋልሃል ፤ በሰው በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ ይሆንልሃል። /1ኛ ሳሙ 17፤34-54/ ልጆች ቢኖሩህ ምከራቸው ፤ ከሕጻንነታቸው ጀምረህ ሰቢረ ክሳድን አስተምራቸው። /ሲራ 7፤23 ና 17፤1-4/ ወስብሐት ለእግዚአብሔር