ልጅህ


Ø እንደ ቃየል በቅናት ካደገ የገዛ ወንድሙን ይገድላል። /ዘፍ 4፤5/


Ø እንደ ካም ካደገ ያንተኑ ሃፍረት ይገልጥብሃል።
/ዘፍ 9፤21-22/

Ø እንደ ዲና ካደገች ሂዳ ከጠላቶችህ ትወዳጃለች።
/ዘፍ 34፤1/

Ø እንደ ዔሳው ካደገ ምቀኛ ይሆንብሃል።
/ዘፍ 27፤41-45/

Ø እንደ ይሁዳ ልጆች ካደገ የከፋ ይሆንብሃል።
/ዘፍ 38፤1-11/

Ø እንደ ሮቤል ካደገ ሚስትህን ይቀማሃል።
/ኩፍ 28፤35-44/

Ø እንደ አፍኒንና ፊንሐስ ካደገ ታቦት ሻጭ ይሆንብሃል።
/1ኛ ሳሙ 2፤12/

Ø እንደ አምኖን ከደገ የገዛ እህቱን ይደፍርብሃል።
/2ኛ ሳሙ 13፤1-19/

Ø አንደ አቤሴሎም ካደገ አንተንም ያሳድድሃል።
/2ኛ ሳሙ 17፤21-24/

Ø አንደ ሴምና ያፌት ከደገ ሃፍረትህን ይደብቅልሃል።
/ዘፍ 9፤23/

Ø አንደ ዮሴፍ ካደገ በችግርህ ደራሽ ይሆንልሃል።
/ዘፍ 39፤7-23/

Ø እንደ ይስሐቅ ካደገ ታማኝ ሆኖ ራሱን ይሰዋል።
/ዘፍ 22፤9/

Ø እንደ ሳሙኤል ካደገ የእግዚአብሔር ሰው ይሆንልሃል።
/1ኛ ሳሙ 3፤17-20/

Ø እንደ ዳዊት ካደገ የአገርህን ጠላት ያጠፋልሃል ፤ በሰው
በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ ይሆንልሃል። /1ኛ ሳሙ 17፤34-54/

ልጆች ቢኖሩህ ምከራቸው ፤ ከሕጻንነታቸው ጀምረህ ሰቢረ ክሳድን አስተምራቸው።
/ሲራ 7፤23 ና 17፤1-4/
ወስብሐት ለእግዚአብሔር


Comments

  1. ልጅ ስላለኝ ነው መሰለኝ የመጀመርያዎቹ ባሕርይዎች ዘገነኑኝ፤ አጥንቴን ሁሉ ቀዘቀዘኝ፡፡ ደግነቱ የመጨረሻዎቹ ልጆች መልሰው አጽናኑኝ፡፡ ነገሩ ግን ይገርማል፡፡

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular posts from this blog

ቅዱስ ያሬድ ማነው? ከዳንኤል ክብረት

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፬ የሐዲስ ኪዳን መግቢያ

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፪