Posts

Showing posts from August, 2011

ደብረ ታቦር

Image
ይህ በዓል በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ የሚከበር ሲሆን ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ አያሰተማረ በነበረበት ዘመን በደብረ ታቦር ላይ ብርሃነ መለኮቱን ክበረ መንግስቱን የገለጸበት እለት ነው። /ማቴ ፲፯፥፩/ ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ ልዩ ስም አለው ቡሄ ይሉታል ቡሄ ማለት መላጣ ገላጣ ማለት ሲሆን ይህን ስያሜ ያገኘው ክረምቱ አልቆ ደመናው ተገልጦ ብርሃን የሚታይበት ጊዜ ስለሆነ ነው ተብሎ ይነገራል። ነገር ግን የደብረ ታቦር ምስጢር የተገለጸው በፍልስጥኤም ደመና በማይታይበት በበጋ ወራት ነው።