Posts

Showing posts from 2017

Muaze Tibrbat D/n Daniel Kibret

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፪

Image
የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፡፡ነገር ግን ከራሳቸው አመንጭተው ሳይሆን በእግዚአብሔር ተልከው በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ጽፈውታል፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነው፡፡ በውስጡ የያዛቸው ቅዱሣት መጻሕፍት ከአምላካችን ከእግዚአብሔር የተገኙ መጻሕፍት አምላካዊያት ይባላሉ ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ ስለመጻፉ የሚከተሉትን ጥቅሶች እንመለከታለን፡፡ 1.       2ኛ ሳሙ 23፡2 2.      2ኛ ጢሞ 3፡16 3.      2ኛ ጴጥ 1፡2ዐ በመንፈስ ቅዱስ ተመርተውና ተነድተው መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉ ሰዎች ከተለያየ የሥራ መስክ የተጠሩ ናቸው፡፡ እንዲሁም በተለያየ ዘመን ነበር፡፡ ሆኖም የጻፉአቸውን መጻሕፍት ያስጻፉዋቸው አንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ ቃሌም ሆነ መልዕክቱ ፈጽሞ አይጋጭም /አይጣላም/፡፡ ጸሐፊዎቹ በችሎታቸው በዕውቀታቸው የተለያዩ ሆነው ሳለ በእግዚአብሔር መንፈስ የጻፉአቸው ቅ/መጻሕፍት ግን ዋና ሐሳባቸው እና መልዕክታቸው አልተለያየም፡፡ በዚህም ምክንያት እኛ ለሕይወታችን መመሪያ መጽሐፍ ቅዱስን የበላይ አድርገን ተቀብለንዋል ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ይባላል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖናዊነቱ ቀኖና የሚለው ቃል ካኖን የሚለውን የግሪከኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙም መለኪያ ዘንግ ማለት ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ስንልም መጽሐፍ የያዘውን የመጻሕፍት ቁጥር/ብዛት/ ያመለክታል፡፡ እንደሚታወቀው መጽሐፍ ቅዱስ የብሉኪዳንና የአዲስ ኪዳንን መጻሕፍት የያዘ ሲሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ.ክ.ቀኖና መሠረት ብ.ኪዳን 46 አ.ኪዳ...

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፩

Image
መጽሐፍ ቅዱስ ምንድን ነው?   መጽሐፍ ቅዱስ ማለት ቅዱስ ማጽሐፍ ማለት ነው፡፡ በራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህን በተመለተ ‹‹ ቅዱሳን መጻሕፍት ›› የሚል ንባብ ይገኛል፡፡ ሁለቱን እንደሚከተለው እናያለን፡፡ 1.       ‹‹ ….በነቢያቱ እና በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ወንጌል ለእግዚአብሔር ተለየ፡፡ ›› /ሮሜ 1.2/ 2.      ‹‹ …. ከህፃንነትህ ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል ›› /2ጢሞ 3፡15/ ከስያሜው እንደምንረዳው መጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ነው፡፡ ቅዱስ የተባለበት   ምክንያትም፡- 1.       ቅዱስ ማለት የተለየ፣ ክቡር ማለት ሲሆን ከርኩሳንና ከተናቁ መጻሕፍት የተለየ ስለሆነ 2.      ከቅዱስ እግዚአብሔር የተገኘ ቃልን የያዘ መጽሐፍ ስለሆነና ቃሉን የሚጠብቁትን ምዕመናንን የሚቀድስ ስለሆነ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ይህም ማለት ለሰው ዘር ሁሉ እውነተኛ የእግዚአብሔርን የማዳን መልዕክት የያዘ መጽሐፍ ነው ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃልም፡- 1.       ዘለዓለማዊ ነው፡፡  /ኢሳ 40፡8፡፡ ማቴ 24፡35/ 2.      የመንፈስ ሠይፍ ነው /ኤፌ 6፡17/ 3.      የሚሠራ ሕያው ነው /ዕብ 4፡12/ 4.     የሰው ልጆች ዳግመኛ የሚወለዱበት ከማይጠፋ ዘር ነው፡...