መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፫
የመጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈል፡-
መጽሐፍ ቅዱስ ባጠቃላይ በሁለት ታላላቅ ክፍሎች ይከፈላል
1.
ብሉይ ኪዳን፡- ከክርስቶስ ልደት በፊት የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው በአብዛኛው የተፃፉት በነበያት ነው፡፡
2.
አዲስ ኪዳን፡- ከክርስቶስ ልደት በኋላ በሐዋርያት የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ
ከያዘው ቃል አንፃር በዘመናት ሲታይ በሦስት ይከፈላል፡፡
1. ዘመነ አበው፡- በኦሪት ዘፍጥረት
የተገለጠው ነው፡፡
2. ዘመነ ኦሪት ፡- ከኦሪት ዘጸአት እስከ ትንቢተ ሚልክያስ ድረስ ድረስ የተገለጠው
ነው፡፡
3. ዘመነ ክርስትና /ወንጌል/፡- በአዲስ
ኪዳን መጻሕፍት የተመዘገበው ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ለመጥቀስ አመቺ እንዲሆን በውስጡ የያዛቸው ቅ/መጻሕፍት እያንዳንዳቸው በምዕራፍና
በቁጥር ተከፍለዋል፡፡ ከጥንት ጀምሮ ቅዱሳት መጻሕፍተን የሚገለብጡ ሰዎች ምዕራፍና ቁጥር ለማውጣት ሞክረዋል፡፡ ነገር ግን እንደገና
አሁን ባለው መልኩ የተከፈለው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
1. በምዕራፍ የተከፈለው በ1228 ዓ.ም
ሲሆን የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ በነበረው በስቴፈን ላንግተን አማካይነት ነው፡፡
2. ምዕራፍ በቁጥር የተከፈለው ደግሞ
በ1551 ዓ.ም ሲሆን ሮበርት ናታን (ስቴፋነስ) በተባለው የፈረንሳይ ሰው አማካይነት ነው፡፡
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በምዕራፍና በቁጥር ለመጥቀስ ሲያስፈልግ ሥርዓተ ነጥቦችንና የምህፃረ ቃላት ምልክቶችን /መሪ
ምልክቶችን/ በተመለከተ፣ እንዲሁም ስለ ጥቅሶች ቁርኝት የተሰጠውን መግለጫ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም መግለጫ የሚገኘው በመጽሐፍ
ቅዱስ መካከል በአ.ኪ. መግቢያ የመጀመሪያ ቅጠል ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት ቋንቋ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብሉየ ኪዳን
መጻሕፍት በመጀመሪያ በዕብራይስጥ ቋንቋ የተጻፈ ሲሆን ጥቂት ክፍሎች ግን በአራማይክ ቋንቋ እንደተጻፉ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ የአዲስ
ኪዳን መጻሕፍት ደግሞ የማቴዎስ ወንጌል በዕብራይስጥ፣ የማርቆስ ወንጌል በሮማይስጥ /ላቴን/ የተጻፉ ሲሆን የቀሩት በዘመነ
ስልጣኔ የአብዛኛው ሕዝብ መነጋገሪያ በነበረው በግሪክ /ጽርዕ/ ቋንቋ ተጽፈዋል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ ከተጻፈባቸው
ቋንቋዎች ወደተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉመዋል፡፡ ከነዚህም 4ቱን ብቻ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡
1. ወደ ግሪከኛ፡- የብሎይ ኪዳን መጻሕፍት ወደ ግሪከኛ
ቋንቋ የተተረጐሙት በ285 ቅ.ል.ክ. በሰባሊቃናት
አማካኝነት ነው፡፡
እንዲተረጐም ያዘዘውም ንጉሥ ዳግማዊ በጥሊሞስ ፊላድልፎስ የተባለው ንጉሥ ነው የተተረጐመው በእስክንድርያ ከተማ ነው
ይህም ሰኘቱስጌንታ በመባል ይታወቃል፡፡
2.
ወደ ላቲን፡- መጽሐፍ ቅዱስን ወደላቲን ቋንቋ የተረገመው አባዦሮም የተባለው የላቲን ቤ.ክ አባት ነው
ዘመኑም በ42ዐ ዓ.ም. ነው የተረገመውም በፖፖ ዳማሶስ ሲሆን የተተረጐመበትም ዋሻ ነው ትርጉሙም ቬልቲጋ በመባል ይታወቃል፡፡
3.
ወደግእዝ፡- እስከ ሰለሞን ድረስ የተጻፉት
የብ.ኪ. መጻሕፍተ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1000 ዓመት በንግሥተ ሳባ ዘመን ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር በመጡት ሌዋውያንና በኢትዮጵያን
ሊቃውንት አማካይነት ወደግእዝ ተተጉመዋል፡፡ ከዚህ ወዲህ የተጻፉትም በየጊዜው ተተርጉመዋል፡፡ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ደግሞ ለመጀመሪያ
ጊዜ ከግሪክ ወደ ግእዝ የተተረጐሙት በ4ኛው ክ/ዘመን ሲሆን በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን አማካኝነት ነው ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ
ወደ ግእዝ የተተረጐመው በ5ኛው ክ/ዘመን በተሳወቁ ቅዱሳን አማካኝነት ነው የተሰዐቱ ቅዱሳን ትርጉም የተተረገመው ሙሉ በሙሉ ከግሪከኛ
ቋንቋ ነው፡፡
4.
ወደአማርኛ ፡- ቀደም ባለው ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ
ወደ አማርኛ ይተረጐም የነበረው በእንድምታ ትርጓሜ በሚደክሙ ኢትዮጵያዊያን ሊቃውንት ነበር ይኸውም ግእዙን በአንድምታ ትርጓሜ ወደ
አማርኛ በመተርጐም ነበር፡፡ ነገር ግን ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን በነጠላ ትርጓሜ ለመጀመሪያ ጊዜ የተተረጐመው አባሮሜ/ በኢትዮጵያዊ
ስሙ አባ አብርሃም/ ነው፡፡ የተረጐመውም ከ18ዐ8-1818 ዓ.ም እ.ኤ.አ. ባሉት 1ዐ ዓመታት ውስጥ ነው የተረጐመበት ቦታም በግብፅ
ዋና ከተማ በካይሮ ውስጥ ነው፡፡ ይህም ትርጉም በእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር በኩል በተለያየ ጊዜ በየከፊሉና በሙሉ ታትሟል፡፡
ይኸውም፡-
1.
በ1824 ዓ.ም. 4ቱ ወንጌላት
2. በ1819 ዓ.ም. አዲስ ኪዳን
3. በ184ዐ ዓ.ም ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ታትሟል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በብዛት በሰው እጅ
የሚገኘው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ የታተመው በ1954 ዓ.ም. ሲሆን በቀ.ኃ.ሥ. ትእዛዝ መሠረት በተቋቋመ የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጉም
ሊቃውንት በሚገኝበት ኮሚቴ አማካኝነት ነው፡፡
በጥቂት ዓመታት እንደታወቀው ባጠቃላይ
መጽሐፍ ቅዱስ በዘመናችን ከ15ዐዐ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የተተረጐመ ሲሆን በአገራችን እስከአሁን ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ የተተረገመው
በግእዝ፣ በአማርኛ፣ በትግሪኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎች ብቻ ነው፡፡ ከ2ዐ በሚበልጡ በሌሎቹ የአገራችን ቋንቋዎች ግን በየከፊሉ እየተተረጐመ
ታትሟል፡፡ በየቋንቋው መተርጐሙ የእግዚአብሔር ቃል በሁሉም ቦታና ብሔር እንዲዳረስ የሚያደርግ ነው፡፡
Comments
Post a Comment