Posts

Showing posts from 2021

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፬ የሐዲስ ኪዳን መግቢያ

Image
የሐዲስ ኪዳን መግቢያ   ሐዲስ ኪዳን   -         ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው ግስ የመጣ የግእዝ ቃል ነው፡፡ ‹‹ ተካሄደ ›› ማለት ተዋዋለ፣ ተስማማ፣ ተማማለ ማለት ሲሆን ኪዳን ማለትም ውል ፣ ስምምነት ፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ -         ኪዳን በሁለት ወገኖች መካከል የሚመሠረት ውል ሲሆን ከተመሠረተ በኋላ በሁለቱ ወገኖች መካከል እንደ ሕግ ሆኖ የሚመሠረት ስምምነት ነው፡፡ -         በመጽሐፍ ቁጥስ ውስጥ ኪዳን ሲባል ከእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠና ሰዎች በእምነት የተቀበሉት ውል ነው፡፡ -         ሐዲስ ኪዳን ከእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠ የድኀነት ኪዳን ነው፡፡ ይኸውም በወልደ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንሚያገኝ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ -         የዚህ ድኅነት ኪዳን ቃላትም፡- ·        ያመነ የተጠመቀም ይድናል፣ /ማር16÷16/ ·        በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው /ዮሐ 3÷36/ ·        እውነት እውነት እላችኋላሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው     /ዮሐ 6÷47/ ·        ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃ...